ታማኙ ኢዮብ ሥቃይ እንደበዛበት ተናገረ
ኢዮብ ቢደኸይ፣ ሐዘን ቢያደቀው እንዲሁም ከባድ በሽታ ቢይዘውም እንኳ ታማኝነቱ ጠብቋል። ስለዚህ ሰይጣን ኢዮብን ተስፋ በማስቆረጥ ንጹሕ አቋሙን እንዲያጎድፍ ለማድረግ ሞከረ። ሦስቱ የኢዮብ “ጓደኞች” መጡ። መጀመሪያ ያዘኑ ለመምሰል ሞከሩ። ከዚያም አንድ የሚያጽናና ቃል እንኳ ሳይተነፍሱ ለሰባት ቀናት ከኢዮብ ጋር ቁጭ አሉ። ከዚያ በኋላ የተናገሩት ነገርም በክስና በውንጀላ የተሞላ ነበር።