በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 11-15

ኢዮብ በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት ነበረው

ኢዮብ በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት ነበረው

ኢዮብ አምላክ እሱን ከሞት የማስነሳት ችሎታ እንዳለው ተናገረ

14:7-9, 13-15

  • ኢዮብ፣ አምላክ ከሞት እንደሚያስነሳው ያለውን እምነት ለመግለጽ ዛፍን ምናልባትም የወይራ ዛፍን እንደ ምሳሌ ተጠቅሟል

  • የወይራ ዛፍ ሥሩን በስፋት ስለሚዘረጋ ግንዱ ቢደርቅም እንኳ ዛፉ ሊያንሠራራ ይችላል። ሥሮቹ እስካልሞቱ ድረስ ዛፉ እንደገና ያቆጠቁጣል

  • ከከባድ ድርቅ በኋላ ዝናብ ሲጥል፣ ደርቆ የነበረ የወይራ ዛፍ ጉቶ እንደገና ሊያንሰራራ ይችላል፤ ከዛፉ ሥሮች ላይ ቀንበጥ ማቆጥቆጥ ስለሚጀምር ዛፉ ‘እንደ አዲስ ተክል ቅርንጫፎች ያወጣል’