በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | አስቴር 6-10

አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ በመቆርቆር እርምጃ ወስዳለች

አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ በመቆርቆር እርምጃ ወስዳለች

አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ ጥብቅና ስትቆም ደፋርና የራሷን ጥቅም መሥዋዕት የምታደርግ መሆኗን አሳይታለች

8:3-5, 9

  • አስቴርና መርዶክዮስ ከሞት ተርፈዋል። ይሁን እንጂ ሃማ አይሁዳውያንን በሙሉ ለመፍጀት ያወጣው አዋጅ በፋርስ ግዛት ውስጥ ከዳር እስከ ዳር እየተዳረሰ ነበር

  • አስቴር ለሁለተኛ ጊዜ ሕይወቷን አደጋ ላይ በመጣል ሳትጠራ ንጉሡ ፊት ቀረበች። ንጉሡ እግር ላይ ወድቃ ስለ ሕዝቧ በማልቀስ የወጣውን አሰቃቂ አዋጅ እንዲሽር ለመነች

  • በንጉሡ ስም የተላለፈ ሕግ ሊሻር አይችልም። ስለዚህ ንጉሡ አዲስ ሕግ እንዲያጸድቁ ለአስቴርና ለመርዶክዮስ ሥልጣን ሰጣቸው

ይሖዋ ለሕዝቡ ታላቅ ድል ሰጣቸው

8:10-14, 17

  • አይሁዳውያን ራሳቸውን የመከላከል መብት እንዳላቸው የሚገልጽ ሁለተኛ አዋጅ ወጣ

  • ፈረሰኞች በግዛቱ ውስጥ ወዳሉት ስፍራዎች ሁሉ በፍጥነት ሄዱ፤ አይሁዳውያንም ለጦርነት ተዘጋጁ

  • ብዙ ሰዎች አምላክ አይሁዳውያንን እንደረዳቸው በመገንዘብ የአይሁድ እምነትን ተቀበሉ