በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እንግዶቻችንን መቀበል

እንግዶቻችንን መቀበል

መጋቢት 23 ከ12 ሚሊዮን የሚበልጡ እንግዶች በመታሰቢያው በዓል ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል። ንግግር የሚያቀርበው ወንድም ይሖዋ ስላዘጋጀልን ቤዛ እንዲሁም በቤዛው ምክንያት የሰው ልጆች ስለሚያገኟቸው አንዳንድ በረከቶች ስለሚጠቅስ ለእነዚህ ሰዎች አስደናቂ ምሥክርነት ይሰጣል። (ኢሳ 11:6-9፤ 35:5, 6፤ 65:21-23፤ ዮሐ 3:16) ይሁንና በዚህ ለየት ያለ ዝግጅት ላይ ምሥክርነት የሚሰጠው ተናጋሪው ብቻ አይደለም። ሁላችንም እንግዶቻችንን ሞቅ ባለ ስሜት በመቀበል ግሩም ምሥክርነት መስጠት እንችላለን። (ሮም 15:7) ይህን ለማድረግ የሚረዱ አንዳንድ ሐሳቦች ቀጥሎ ቀርበዋል።

  • ቦታችን ላይ ተቀምጠን ፕሮግራሙ እስኪጀምር ከመጠበቅ ይልቅ እንግዶችንና የቀዘቀዙ አስፋፊዎችን በፈገግታ እንቀበል፤ እንዲሁም ለእነሱ ሞቅ ያለ ሰላምታ እንስጣቸው

  • ጋብዘናቸው ለመጡት የምናውቃቸው ሰዎች ለየት ያለ ትኩረት መስጠት ያለብን ቢሆንም መጋበዣው ደርሷቸው የመጡትንም ለመርዳት ንቁ መሆን አለብን። አዳዲሶች አብረዋችሁ እንዲቀመጡ ጋብዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስና መዝሙር መጽሐፍ አብረዋችሁ እንዲከታተሉ አድርጉ

  • ስብሰባው ሲያልቅ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ዝግጁ ሁኑ። ከእናንተ በኋላ በዚያው አዳራሽ የመታሰቢያውን በዓል የሚያከብር ሌላ ጉባኤ ካለና አዳራሹን በፍጥነት መልቀቅ የሚጠበቅባችሁ ከሆነ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተገናኝታችሁ ለመነጋገር ቀጠሮ ያዙ። አድራሻው ከሌላችሁ እንዲህ ልትሉት ትችላላችሁ፦ “በዓሉን እንዴት እንዳገኘኸው ብትነግረኝ ደስ ይለኛል። እንዴት መገናኘት እንችላለን?”