በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? የተባለውን ብሮሹር መጠቀም

በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? የተባለውን ብሮሹር መጠቀም

የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? የተባለው ብሮሹር ከተማሪው ጋር ከእያንዳንዱ ጥናት በፊት ወይም በኋላ እንድንወያይበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። * ከትምህርት 1 እስከ 4 ያሉት የብሮሹሩ ክፍሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የይሖዋ ምሥክሮች ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ እንዲያውቁ፣ ከትምህርት 5 እስከ 14 ያሉት ክፍሎች እንቅስቃሴያችን ምን እንደሚመስል እንዲገነዘቡ፣ ከትምህርት 15 እስከ 28 ያሉት ክፍሎች ደግሞ ድርጅታችን ምን እንደሚያከናውን እንዲማሩ የሚረዱ ናቸው። አስቀድማችሁ ልትወያዩበት የምትፈልጉት ርዕስ ከሌለ በስተቀር በጥቅሉ ሲታይ ብሮሹሩን በቅደም ተከተል ማጥናቱ የተሻለ ነው። እያንዳንዱ ትምህርት አንድ ገጽ የሚሸፍን ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከአምስት እስከ አሥር ደቂቃ ሊወስድ ይችላል።

  • ተማሪው በጥያቄው ላይ ማለትም በትምህርቱ ርዕስ ላይ እንዲያተኩር አድርጉ

  • ትምህርቱን በአንድ ጊዜ ወይም ከፋፍላችሁ አንብቡ

  • ባነበባችሁት ላይ ከተማሪው ጋር ተወያዩ። በገጹ ግርጌ ላይ በሚገኙት ጥያቄዎችና በሥዕሎቹ ላይ ተወያዩ። እንደ አስፈላጊነቱ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተገለጹ ጥቅሶችን አንብባችሁ ተወያዩባቸው። በደማቁ የተጻፉት ንዑስ ርዕሶች ለዋናው ጥያቄ መልስ የሚሰጡት እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርጋችሁ ግለጹ

  • በትምህርቱ ላይ “ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት” የሚል ሣጥን ካለ ተማሪው በሣጥኑ ውስጥ የቀረቡትን ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርግ አበረታቱት

^ አን.3 ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰው የዚህ ብሮሹር ቅጂ የሚገኘው በኤሌክትሮኒክ ቅጂው ላይ ነው።