በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

ጥያቄ፦ አምላክ ከሰጠን ስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ የትኛው ይመስልሃል?

ጥቅስ፦ ዮሐ 3:16

አበርክት፦ ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ፣ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ እንዲሞትልን ያደረገው ለምን እንደሆነና ለዚህ ስጦታ ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? T-36

ጥያቄ፦ [የትራክቱን የፊት ገጽ አሳይ።] ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ትሰጣለህ? የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ልባችን ውስጥ ያለ ነገር? ምሳሌያዊ ነገር? ወይስ በሰማይ ያለ መስተዳድር?

ጥቅስ፦ ዳን 2:44፤ ኢሳ 9:6 ግርጌ

አበርክት፦ ይህ ትራክት፣ የአምላክን መንግሥት ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልህ ያብራራል።

የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ

አበርክት፦ ሰዎችን በአንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ እየጋበዝን ነው። [መጋበዣውን ስጥ።] በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስን ሞት ለማሰብና የእሱ ሞት የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ የሚያብራራ ንግግር ለማዳመጥ ይሰበሰባሉ፤ በዓሉ የሚከበረው ሚያዝያ 3, 2009 (ሚያዝያ 11, 2017) ነው። ይህ የመጋበዣ ወረቀት በዓሉ የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ ይዟል። እርስዎም ቢገኙ ደስ ይለናል።

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።