በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጋቢት 27–ሚያዝያ 2

ኤርምያስ 12-16

ከመጋቢት 27–ሚያዝያ 2
  • መዝሙር 128 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • እስራኤል ይሖዋን ረስቷል”፦ (10 ደቂቃ)

    • ኤር 13:1-5—ኤርምያስ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ቢጠይቅበትም ከተልባ እግር የተሠራውን ቀበቶ እንዲደብቅ አምላክ የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሟል (jr-E 51 አን. 17)

    • ኤር 13:6, 7—ኤርምያስ ረጅም ጉዞ አድርጎ ቀበቶውን ለማምጣት ሲሄድ ቀበቶው ተበላሽቶ አገኘው (jr-E 52 አን. 18)

    • ኤር 13:8-11—ይሖዋ ይህን ምሳሌ የተጠቀመው እስራኤላውያን ግትር በመሆናቸው ምክንያት ከእሱ ጋር ያላቸው የጠበቀ ግንኙነት እንደሚበላሽ ለማስረዳት ነበር (jr-E 52 አን. 19-20it-1-E 1121 አን. 2)

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

    • ኤር 12:1, 2, 14—ኤርምያስ ምን ጥያቄ አቅርቦ ነበር? ይሖዋስ ምን ምላሽ ሰጠው? (jr-E 118 አን. 11)

    • ኤር 15:17—ኤርምያስ ስለ ባልንጀርነት ምን አመለካከት ነበረው? እኛስ እሱ የተወውን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (w04 5/1 12 አን. 16)

    • የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?

    • የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ኤር 13:15-27

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ እና ቪዲዮ—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ እና ቪዲዮ—ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • ንግግር፦ (6 ደቂቃ) w16.03 29-31—ጭብጥ፦ ታላቂቱ ባቢሎን የአምላክን ሕዝቦች በምርኮ ይዛ የነበረው መቼ ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት