በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ቤተሰባችሁ ይሖዋን እንዳይረሳ እርዱ

ቤተሰባችሁ ይሖዋን እንዳይረሳ እርዱ

ኤርምያስ አይሁዳውያን አምላካቸውን ይሖዋን በመርሳታቸው ጥፋት እንደሚመጣባቸው እንዲያስጠነቅቅ ተልእኮ ተሰጥቶት ነበር። (ኤር. 13:25) ብሔሩ እንዲህ ያለ አሳዛኝ መንፈሳዊ ሁኔታ ውስጥ የገባው እንዴት ነው? በእስራኤል የነበሩ ቤተሰቦች መንፈሳዊነታቸውን አጥተው ነበር። ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው የቤተሰብ ራሶች ይሖዋ በዘዳግም 6:5-7 ላይ የሰጠውን መመሪያ መከተል አቁመው ነበር።

በዛሬው ጊዜም ለጠንካራ ጉባኤዎች መሠረት የሚሆኑት ጠንካራ ቤተሰቦች ናቸው። የቤተሰብ ራሶች ቋሚና ትርጉም ያለው የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም እንዲኖር በማድረግ ቤተሰቡ ይሖዋን እንዳይረሳ መርዳት ይችላሉ። (መዝ 22:27) እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ”—ከቤተሰቦች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ የሚለውን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሞክሩ፦

  • አንዳንድ ቤተሰቦች ከቤተሰብ አምልኮ ጋር በተያያዘ ብዙዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች መወጣት የቻሉት እንዴት ነው?

  • ቋሚና ትርጉም ያለው የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም መኖሩ የሚያስገኛቸው አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

  • የቤተሰብ አምልኮ ፈታኝ እንዲሆንብኝ እያደረጉ ያሉት ችግሮች የትኞቹ ናቸው? እነዚህን ችግሮች ለመወጣት ምን እርምጃ መውሰድ እችላለሁ?