በስሎቬንያ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ መጋበዝ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ መጋቢት 2018

የውይይት ናሙናዎች

‘ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?’ እና ‘ቤዛው ምን ጥቅም ያስገኝልናል?’ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ የተመሠረቱ ውይይቶች።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል”

የሰዎችን ትኩረት በሚስቡና በሌሎች ዘንድ አድናቆት እንድናተርፍ በሚያደርጉ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የማተኮር ዝንባሌ አለን? ትሑት የሆነ አገልጋይ አብዛኛውን ጊዜ ይሖዋ ብቻ ሊያየው የሚችለውን ሥራ ይሠራል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ሁለቱን ታላላቅ ትእዛዛት ጠብቁ

ኢየሱስ እንደተናገረው ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት የትኞቹ ናቸው? እነዚህን እንደምናከብር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለአምላክና ለባልንጀራችን ፍቅር ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?

ለአምላክና ለባልንጀራችን ፍቅር ሊኖረን ይገባል። ይህን ፍቅር ልናዳብር የምንችልበት አንዱ ወሳኝ መንገድ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ነው።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

በመጨረሻዎቹ ቀናት ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁዎች ሁኑ

በዛሬው ጊዜ ያሉት አብዛኞቹ ሰዎች በዕለት ተዕለት የኑሮ ጉዳዮች ከመጠመዳቸው የተነሳ ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረት መስጠት ተስኗቸዋል። በመንፈሳዊ ንቁ የሆኑ ክርስቲያኖች ከዓለም የሚለዩት እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ ቀርቧል

ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ የምንኖረው መጨረሻው በጣም በቀረበበት ጊዜ ላይ እንደሆነ የሚጠቁመው እንዴት ነው? የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ ቀርቧል የተባለው ቪዲዮ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”

ስለ አሥሩ ደናግል በሚናገረው ምሳሌ ላይ ሙሽራው፣ ልባሞቹ ደናግል እና ሞኞቹ ደናግል ማንን ያመለክታሉ? ይህ ምሳሌ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥናቶቻችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ማሳየት

ከጅምሩ አንስቶ ጥናቶቻችን ተዘጋጅቶ የመምጣት ልማድ እንዲያዳብሩ ልንረዳቸው ይገባል። ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?