በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 25

“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”

“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”

25:1-12

ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል የሚናገረውን ምሳሌ የጠቀሰው ለቅቡዓን ተከታዮቹ ቢሆንም መሠረታዊ ሐሳቡ ለሁሉም ክርስቲያኖች ይሠራል። (w15 3/15 12-16) “ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” በማለት ተናግሯል። (ማቴ 25:13) ኢየሱስ የተናገረውን ይህን ምሳሌ ማብራራት ትችላለህ?

  • ሙሽራው (ቁጥር 1)—ኢየሱስ

  • ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩት ልባሞቹ ደናግል (ቁጥር 2)—የተሰጣቸውን ሥራ በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ የሆኑትና እስከ መጨረሻው ድረስ እንደ ብርሃን አብሪዎች የሚያበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች (ፊልጵ 2:15)

  • “ሙሽራው እየመጣ ነው” የሚለው ጫጫታ (ቁጥር 6)—የኢየሱስን መገኘት የሚያሳውቁ ማስረጃዎች

  • ሞኞቹ ደናግል (ቁጥር 8)—ሙሽራውን ለመቀበል ቢወጡም እስከ መጨረሻው ንቁዎች ያልሆኑና ንጹሕ አቋማቸውን ያልጠበቁ ቅቡዓን ክርስቲያኖች

  • ልባሞቹ ደናግል ዘይታቸውን ለመስጠት ፈቃደኞች አለመሆናቸው (ቁጥር 9)—የመጨረሻው ማኅተም ከተደረገ በኋላ ታማኞቹ ቅቡዓን፣ ታማኝነታቸውን ያጓደሉትን ቅቡዓን መርዳት አይችሉም፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ የሚችሉበት ጊዜ አልፏል

  • ‘ሙሽራው መድረሱ’ (ቁጥር 10)—ወደ ታላቁ መከራ ማብቂያ አካባቢ ኢየሱስ ፍርድ ለመስጠት ይመጣል

  • ልባሞቹ ደናግል ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ድግስ መግባታቸው፤ ከዚያም በሩ መዘጋቱ (ቁጥር 10)—ኢየሱስ ታማኝ ቅቡዓኑን ወደ ሰማይ ይሰበስባቸዋል፤ ታማኝ ያልሆኑት ቅቡዓን ግን ሰማያዊ ሽልማታቸውን ያጣሉ