በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥናቶቻችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ማሳየት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥናቶቻችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ማሳየት

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን ተዘጋጅተው የሚመጡ ከሆነ የምናስተምራቸውን ነገር በቀላሉ መረዳትና ማስታወስ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ፈጣን እድገት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል። ከተጠመቁ በኋላም ቢሆን ‘ዘወትር ነቅተው መጠበቅ’ እንዲችሉ ለስብሰባዎችና ለአገልግሎት መዘጋጀት ያስፈልጋቸዋል። (ማቴ 25:13) በመሆኑም እንዴት ማጥናት እንደሚችሉ ማወቃቸውና ጥሩ የጥናት ልማድ ማዳበራቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይጠቅማቸዋል። ከጅምሩ አንስቶ ጥናቶቻችን ተዘጋጅቶ የመምጣት ልማድ እንዲያዳብሩ ልንረዳቸው ይገባል።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ጥሩ ምሳሌ ሁኑ። (ሮም 2:21) የጥናታችሁን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዱ የጥናት ፕሮግራም ተዘጋጁ። (km 11/15 3) ጥናታችሁ የተዘጋጃችሁበትን ጽሑፍ እንዲያይ አድርጉ

  • ጥናታችሁን እንዲዘጋጅ አበረታቱት። በቋሚነት ማጥናት ከጀመራችሁበት ጊዜ አንስቶ፣ ተዘጋጅቶ መምጣት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራሙ ክፍል እንደሆነና እንዲህ ማድረግ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት እንዲያስተውል እርዱት። የሚዘጋጅበት ጊዜ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን ስጡት። አንዳንድ አስጠኚዎች ጥናታቸው ተዘጋጅቶ መምጣት ያለውን ጥቅም እንዲያስተውል ለመርዳት ሲሉ በአንዱ የጥናት ፕሮግራም ላይ እነሱ የተዘጋጁበትን ጽሑፍ ይዞ እንዲከታተል ያደርጋሉ። ጥናታችሁ ተዘጋጅቶ ሲመጣ አመስግኑት

  • እንዴት እንደሚዘጋጅ አሳዩት። አንዳንድ አስጠኚዎች ገና ከጅምሩ መላውን የጥናት ክፍለ ጊዜ ተጠቅመው እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ለጥናቶቻቸው ያሳያሉ