በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በቪዲዮ ተጠቅማችሁ አስተምሩ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በቪዲዮ ተጠቅማችሁ አስተምሩ

ሰዎችን በምናስተምርበት ጊዜ በሚታዩ ነገሮች መጠቀማችን፣ የሰዎቹን ትኩረት ለመሳብ የሚረዳ ከመሆኑም ሌላ የተማሩትን ነገር መረዳትና ማስታወስ እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ታላቅ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ በጣም አስፈላጊ ትምህርቶችን ለማስተማር በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሟል። (ዘፍ 15:5፤ ኤር 18:1-6) ኢየሱስም ቢሆን በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ አስተምሯል። (ማቴ 18:2-6፤ 22:19-21) በሚታዩ ነገሮች ተጠቅመን ማስተማር ከምንችልባቸው መንገዶች አንዱ ቪዲዮ ማሳየት ነው፤ ቪዲዮዎች በጣም ጠቃሚ የማስተማሪያ ዘዴዎች መሆናቸው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየታየ ነው። አንተስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችህን ስታስጠና ቪዲዮዎችን ትጠቀማለህ?

ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ስናስጠና እንድንጠቀምባቸው ታስበው የተዘጋጁ አሥር ቪዲዮዎች አሉ። የአብዛኞቹ ቪዲዮዎች ርዕስ፣ በብሮሹሩ ውስጥ ከሚገኙት በደማቅ ፊደላት የተጻፉ ጥያቄዎች ጋር ተመሳሳይ ነው። jw.org ላይ የሚገኘው የዚህ ብሮሹር ቅጂ፣ ቪዲዮዎቹን መቼ ማሳየት እንዳለብን የሚጠቁሙ ሊንኮች ይዟል። በተጨማሪም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ባሉት ጽሑፎቻችን ስናስጠና ልንጠቀምባቸው የምንችል ሌሎች ቪዲዮዎች አሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ለመረዳት ሊከብደው በሚችል ርዕስ ላይ እየተወያያችሁ ነው? አሊያም ደግሞ ጥናትህ በሕይወቱ ውስጥ አንድ ዓይነት ፈተና አጋጥሞታል? jw.org/am ወይም JW ብሮድካስቲንግ ላይ ከሚገኙት ቪዲዮዎች መካከል ለጥናትህ ተስማሚ የሆነውን ምረጥ። ከጥናትህ ጋር ሆናችሁ ቪዲዮውን ከተመለከታችሁ በኋላ ልትወያዩበት ትችላላችሁ።

በየወሩ አዳዲስ ቪዲዮዎች ይወጣሉ። ቪዲዮዎቹን ስትመለከት፣ ሌሎችን ለማስተማር እንዴት ልትጠቀምባቸው እንደምትችል አስብ።