በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የውይይት ናሙናዎች

የውይይት ናሙናዎች

●○○ መመሥከር

ጥያቄ፦ አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

ጥቅስ፦ ዘፍ 1:28

ለቀጣዩ ጊዜ፦ አምላክ ለሰዎች ያለውን ዓላማ እንደሚፈጽም እንዴት ማወቅ እንችላለን?

○●○ የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ አምላክ ለሰዎች ያለውን ዓላማ እንደሚፈጽም እንዴት ማወቅ እንችላለን?

ጥቅስ፦ ኢሳ 55:11

ለቀጣዩ ጊዜ፦ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸዋል?

○○● ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸዋል?

ጥቅስ፦ መዝ 37:10, 11

ለቀጣዩ ጊዜ፦ አምላክ የሚያመጣቸውን በረከቶች ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

የመታሰቢያው በዓል ዘመቻ (ከመጋቢት 23–ሚያዝያ 19)፦

የመጣነው በአንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ ልንጋብዝዎት ነው። የመጋበዣ ወረቀቱ ይኸው። ዓርብ፣ ሚያዝያ 11, 2011 (ሚያዝያ 19, 2019) በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ። ይህ የመጋበዣ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ይገልጻል። በዓሉ ከሚከበርበት ዕለት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ደግሞ “እውነተኛውን ሕይወት ለማግኘት ተጣጣሩ!” የሚል ርዕስ ያለው ንግግር ይቀርባል፤ በዚህም ስብሰባ ላይ ቢገኙ ደስ ይለናል።

ፍላጎት ካሳየ ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?