በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የውይይት ናሙናዎች

የውይይት ናሙናዎች

●○○ መመሥከር

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ማን ነው?

ጥቅስ፦ ማቴ 16:16

ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?

○●○ የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?

ጥቅስ፦ ማቴ 20:28

ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ ለከፈለልን ቤዛዊ መሥዋዕት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

○○● ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ለከፈለልን ቤዛዊ መሥዋዕት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ጥቅስ፦ ዮሐ 17:3

ለቀጣዩ ጊዜ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ምን ይመስላሉ?

የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ (ከመጋቢት 14–ሚያዝያ 7)፦

“የመጣነው በአንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ ልንጋብዝዎት ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ። ይህ በዓል የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ነው።” መጋበዣውን ስጠው። “ይህ የመጋበዣ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ይገልጻል። ከበዓሉ በፊት ባለው ሳምንት ደግሞ ልዩ ንግግር ይኖረናል፤ በዚያም ላይ ቢገኙ ደስ ይለናል።”

ፍላጎት ካሳየ ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?