ከመጋቢት 16-22
ዘፍጥረት 25-26
መዝሙር 18 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ”፦ (10 ደቂቃ)
ዘፍ 25:27, 28—ኤሳውና ያዕቆብ መንትዮች ቢሆኑም ባሕርያቸውም ሆነ ማድረግ የሚያስደስታቸው ነገር የተለያየ ነበር (it-1 1242)
ዘፍ 25:29, 30—ኤሳው ስለራበውና ስለደከመው ራሱን መግዛት አቅቶት ነበር
ዘፍ 25:31-34—ለመንፈሳዊ ነገር አድናቆት ያልነበረው ኤሳው ለአንድ ጊዜ መብል ሲል የብኩርና መብቱን ለያዕቆብ ሸጠ (w19.02 16 አን. 11፤ it-1 835)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)
ዘፍ 25:31-34—ይህ ዘገባ በመሲሑ የዘር ሐረግ ውስጥ የሚካተቱት፣ የብኩርና መብት ያላቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አይደለም የምንለው ለምንድን ነው? (ዕብ 12:16፤ w17.12 15 አን. 5-7)
ዘፍ 26:7—ይስሐቅ በዚህ ወቅት እውነታውን በከፊል የተናገረው ለምንድን ነው? (it-2 245 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋ አምላክን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ዘፍ 26:1-18 (th ጥናት 5)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ የቤቱ ባለቤት የጠየቅነውን ጥያቄ መልስ የማያውቀው ከሆነ እንዳይሸማቀቅ ልንረዳው የምንችለው እንዴት ነው? አስፋፊው ማቴዎስ 20:28ን ውጤታማ በሆነ መንገድ ያብራራው እንዴት ነው?
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። (th ጥናት 3)
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ አበርክት። (th ጥናት 15)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ስታስጠኑ ቪዲዮዎችን ተጠቀሙ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ስንሞት ምን እንሆናለን? እና አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? የተባሉትን ቪዲዮዎች አጫውት። እያንዳንዱን ቪዲዮ ካሳየህ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ስታስጠኑ ይህን ቪዲዮ መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው? (mwb19.03 7) ከዚህ ቪዲዮ ላይ ሌሎችን ለማስተማር የሚረዷችሁ ምን ጠቃሚ ነጥቦች አግኝታችኋል? ምሥራች የተባለው ብሮሹር የኤሌክትሮኒክ ቅጂ የቪዲዮዎቹን ሊንኮች እንደያዘ አድማጮችን አስታውሳቸው።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jy ምዕ. 99
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
መዝሙር 85 እና ጸሎት