በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 25-26

ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ

ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ

25:27-34

ኤሳው ‘ለቅዱስ ነገሮች አድናቆት’ አልነበረውም። (ዕብ 12:16) በዚህም ምክንያት የብኩርና መብቱን ሸጧል። በተጨማሪም ይሖዋን የማያመልኩ ሁለት ሴቶችን አግብቷል።—ዘፍ 26:34, 35

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ከታች ለተጠቀሱት ቅዱስ ነገሮች ከፍተኛ አድናቆት እንዳለኝ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?’

  • ከይሖዋ ጋር ለመሠረትኩት ዝምድና

  • ለመንፈስ ቅዱስ

  • የይሖዋን ቅዱስ ስም የመሸከም መብት

  • ለመስክ አገልግሎት

  • ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች

  • ለትዳር