በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?

ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?

በክልላችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከእኛ ጋር የመታሰቢያውን በዓል እንዲያከብሩ ለመጋበዝ በየዓመቱ ለየት ያለ ጥረት እናደርጋለን። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አብዛኞቹን አናውቃቸውም። ሆኖም የምናውቃቸውን ሰዎችም መጋበዝ ይኖርብናል። ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያውቁት ሰው ከጋበዛቸው በስብሰባው ላይ የመገኘት አጋጣሚያቸው በጣም ሰፊ ነው። (yb08-E 11 አን. 3፤ 14 አን. 1) ታዲያ አንተ እነማንን ልትጋብዝ ትችላለህ?

  • ዘመዶችህን

  • የሥራ ባልደረቦችህን ወይም አብረውህ የሚማሩትን

  • ጎረቤቶችህን

  • ተመላልሶ መጠየቆችህን ወይም ጥናቶችህን (እያስጠናሃቸው ያሉትንም ሆነ ጥናት ያቆሙትን)

በተጨማሪም ሽማግሌዎች የቀዘቀዙ ሰዎችን ለመጋበዝ ጥረት ያደርጋሉ። ልትጋብዘው ያሰብከው ሰው የሚኖረው አንተ ባለህበት አካባቢ ባይሆንስ? በjw.org መነሻ ገጽ ላይ የሚገኘውን ስለ እኛ የሚለውን ክፍል ከፍተህ “የመታሰቢያው በዓል” የሚለውን ጠቅ በማድረግ እሱ በሚኖርበት አካባቢ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ጊዜና ቦታ ማግኘት ትችላለህ። በዚህ ዓመት ለሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ስትዘጋጅ እነማንን መጋበዝ እንደምትችል በጥሞና አስብበት፤ ከዚያም ያሰብካቸውን ሰዎች ጋብዝ።