በ2014 ኒው ጀርሲ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተካሄደ ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ላይ የተገኙ ወንድሞችና እህቶች

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ሚያዝያ 2016

የአቀራረብ ናሙናዎች

ንቁ! መጽሔትና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። እነዚህን ናሙናዎች በመጠቀም የራስን አቀራረብ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ደግነት በተሞላበት መንገድ በመናገር ሌሎችን ማበረታታትና ማጠናከር

ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች እሱን የሚያጽናና ምንም ነገር አልተናገሩም። እንዲያውም እሱን በመወንጀል ጭንቀቱን አባብሰውበታል (ኢዮብ 16-20)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ

“መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?” በሚለው አዲስ ዓምድ ተጠቅመህ በመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ ትችላለህ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢዮብ መጥፎ አስተሳሰቦችን ተዋግቷል

ሰይጣን በሚነዛው ውሸትና ይሖዋ በሚሰማው ስሜት መካከል ያለውን ልዩነት ተመልከት። (ኢዮብ 21-27)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢዮብ ንጹሕ አቋምን በመጠበቅ ረገድ ምሳሌ ነው

ኢዮብ የይሖዋን የሥነ ምግባር መመሪያዎች ለመከተልና የይሖዋን ፍትሕ ለመኮረጅ ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር። (ኢዮብ 28-32)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

እውነተኛ ጓደኛ ገንቢ ምክር ይሰጣል

ኤሊሁ ጓደኛውን ኢዮብን የያዘበትን ፍቅራዊ መንገድ ለመከተል ጥረት አድርግ። (ኢዮብ 33-37)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

ሰዎች በክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የምንጋብዝበት ዘመቻ

የክልል ስብሰባ መጋበዣ ስታሰራጭ ልትዘነጋቸው የማይገቡ ነገሮች። የአቀራረብ ናሙናውን ተለማመድ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

በክልል ስብሰባ ላይ ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምትችልባቸውን መንገዶች ለማሰብ ሞክር።