በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 21-27

ኢዮብ መጥፎ አስተሳሰቦችን ተዋግቷል

ኢዮብ መጥፎ አስተሳሰቦችን ተዋግቷል

ሰይጣን በዛሬው ጊዜ የይሖዋ አገልጋዮችን ተስፋ ለማስቆረጥ ውሸትን እንደ መሣሪያ ይጠቀማል። ሰይጣን በሚነዛው ውሸትና ይሖዋ በሚሰማው ስሜት መካከል ያለው ልዩነት በኢዮብ መጽሐፍ ላይ እንዴት እንደተገለጸ ልብ በል። ይሖዋ ስለ አንተ እንደሚያስብ እርግጠኛ እንድትሆን ያስቻሉህን ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጻፍ።

ሰይጣን የሚያስፋፋቸው ውሸቶች

የይሖዋ ስሜት

አምላክ ከአገልጋዮቹ ብዙ ነገር ስለሚጠብቅ በሚያደርጉት ነገር አይደሰትም። የትኛውም ፍጡር እሱን ማስደሰት አይችልም (ኢዮብ 4:18፤ 25:5)

ይሖዋ የምናደርገውን ልባዊ ጥረት ከፍ አድርጎ ይመለከታል (ኢዮብ 36:5)

ሰው አምላክን ሊጠቅመው አይችልም (ኢዮብ 22:2)

ይሖዋ በታማኝነት የምናቀርበውን አገልግሎት ይቀበላል እንዲሁም ይባርካል (ኢዮብ 33:26፤ 36:11)

አምላክ ጻድቅ መሆን አለመሆንህ ግድ አይሰጠውም (ኢዮብ 22:3)

ይሖዋ ጻድቅ ሰዎችን በትኩረት ይመለከታል (ኢዮብ 36:7)