ከሚያዝያ 18-24
ኢዮብ 28-32
መዝሙር 17 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኢዮብ ንጹሕ አቋምን በመጠበቅ ረገድ ምሳሌ ነው”፦ (10 ደቂቃ)
ኢዮብ 31:1—ኢዮብ ከዓይኑ ጋር “ቃል ኪዳን” ገባ (w15 6/15 16 አን. 13፤ w15 1/15 25 አን. 10)
ኢዮብ 31:13-15—ኢዮብ ትሑት፣ ፍትሐዊና ለሌሎች የሚያስብ ሰው ነበር (w10 11/15 30 አን. 8-9)
ኢዮብ 31:16-25—ኢዮብ ለተቸገሩ ሰዎች በልግስና ይሰጥ ነበር (w10 11/15 30 አን. 10-11)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ኢዮብ 32:2—ኢዮብ “ከአምላክ ይልቅ ራሱን ጻድቅ ለማድረግ” ሞክሯል ሊባል የሚችለው ከምን አንጻር ነው? (w15 7/1 12 አን. 2፤ it-1-E 606 አን. 5)
ኢዮብ 32:8, 9—ኤሊሁ አብረውት ከነበሩት ሁሉ በዕድሜ የሚያንስ ቢሆንም መናገር እንደሚችል የተሰማው ለምንድን ነው? (w06 3/15 16 አን. 1፤ it-2-E 549 አን. 6)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 30:24–31:14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ g16.2 12-13—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል። (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ g16.2 12-13—ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል። (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ bh 148 አን. 8-9 (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መዝሙር 115
ንጹሕ አቋማቸውን ከጠበቁ ሰዎች ትምህርት ማግኘት (1ጴጥ 5:9)፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ሃሮልድ ኪንግ፦ በእስር ቤት ውስጥ በታማኝነት መጽናት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። (tv.pr418.com ውስጥ ቪዲዮ ኦን ዲማንድ > ኢንተርቪውስ ኤንድ ኤክስፒሪየንስስ በሚለው ሥር ይገኛል።) ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ ወንድም ሃሮልድ ኪንግ በእስር ላይ እያለ ታማኝነቱን የጠበቀው እንዴት ነው? በሕይወታችን ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር የሚረዳን እንዴት ነው? ወንድም ሃሮልድ ኪንግ የተወው የታማኝነት ምሳሌ ምን ለማድረግ አነሳስቷችኋል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ia ምዕ. 9 አን. 1-13፤ (30 ደቂቃ)
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 81 እና ጸሎት