በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ

ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ

ከጥር 2016 ጀምሮ ለሕዝብ የሚሰራጨው የመጠበቂያ ግንብ እትም “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?” የሚል ዓምድ በጀርባ ገጹ ላይ ይዞ ይወጣል። ይህ አዲስ ዓምድ የተዘጋጀው በመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለመጀመር እንድንጠቀምበት ነው። ይህ ዓምድ ከትራክቶቻችን ጋር ተመሳሳይ ገጽታ አለው። አንድ የአመለካከት ጥያቄና መጽሐፍ ቅዱስ ለዚያ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ እንዲሁም ለውይይት የሚሆኑ ተጨማሪ ሐሳቦችን ይዟል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ላይ የሚደረጉ ጥሩ ውይይቶች ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ይረዳሉ። ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ረሃባቸውን እንዲያስታግሱ ለመርዳት ይህን አዲስ ዝግጅት በሚገባ እንጠቀምበት።—ማቴ 5:6

ይህን ዓምድ መጠቀም የሚቻልበት መንገድ፦

  1. ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል አንዱን የቤቱን ባለቤት ጠይቅ

  2. አዳምጥ እንዲሁም ለሰጠው መልስ አመስግነው

  3. “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ጥቅስ አንብብ፤ ከዚያም በጥቅሱ ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ ጠይቅ። ግለሰቡ ጊዜ ካለው “መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት

  4. መጽሔቱን አበርክት

  5. ተመልሰህ በመምጣት በሁለተኛው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ