በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 33-37

እውነተኛ ጓደኛ ገንቢ ምክር ይሰጣል

እውነተኛ ጓደኛ ገንቢ ምክር ይሰጣል

ኤሊሁ ኢዮብና ጓደኞቹ እያደረጉ ባለው ውይይት መሃል ሲገባ የሰጠው ምክር ኤሊፋዝ፣ በልዳዶስና ሶፋር ከተናገሩት ፍጹም የተለየ ነበር፤ የምክሩ ይዘትም ሆነ የተሰጠበት መንገድ ከሌሎቹ በጣም የተለየ ነው። እውነተኛ ጓደኛና ጥሩ ምክር ሰጪ መሆኑን አስመሥክሯል፤ ልንከተለው የሚገባ ምሳሌ ትቷል።

ጥሩ ምክር ሰጪ ያሉት ባሕርያት

ኤሊሁ ጥሩ ምሳሌ ትቷል

32:4-7, 11, 12፤ 33:1

 

  • ትዕግሥት

  • ጥሩ አዳማጭ

  • ሌሎችን የሚያከብር

 
  • ኤሊሁ ከመናገሩ በፊት ታላላቆቹ ተናግረው እስኪጨርሱ በትዕግሥት ጠብቋል

  • ምክር ከመስጠቱ በፊት በትኩረት በማዳመጥ ስለ ጉዳዩ ትክክለኛ ግንዛቤ አግኝቷል

  • ኢዮብን በስሙ እየጠራ እንደ ጓደኛ አነጋግሮታል

 

33:6, 7, 32

 

  • ትሑት

  • በቀላሉ የሚቀረብ

  • ሩኅሩኅ

 
  • ኤሊሁ ትሑትና ደግ እንዲሁም ድክመቱን አምኖ የሚቀበል ሰው ነበር

  • ኢዮብ ባጋጠመው መከራ አዝኗል

 

33:24, 25፤ 35:2, 5

 

  • ሚዛናዊ

  • ደግ

  • ነገሮችን በአምላክ ዓይን የሚመለከት

 
  • ኤሊሁ ኢዮብ ሚዛኑን እንደሳተ እንዲገነዘብ በደግነት ረድቶታል

  • ኤሊሁ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የእሱ ጻድቅ መሆን እንዳልሆነ እንዲገነዘብ ኢዮብን ረድቶታል

  • ኤሊሁ የለገሰው ጥሩ ምክር፣ ኢዮብ በኋላ ላይ ይሖዋ የሚሰጠውን ምክር ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆን አድርጎታል