በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

ልክ እንደ ሌሎች ጊዜያት ሁሉ በክልል ስብሰባ ጊዜም ለአምላክና ለሰዎች ያለንን ፍቅር ማሳየት እንፈልጋለን። (ማቴ 22:37-39) አንደኛ ቆሮንቶስ 13:4-8 እንዲህ ይላል፦ “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። . . . ጨዋነት የጎደለው ምግባር አያሳይም፣ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣ በቀላሉ አይበሳጭም። . . . ፍቅር ለዘላለም ይኖራል።” የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች የሚለውን ቪዲዮ ስንመለከት ስብሰባው ላይ ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችልባቸውን መንገዶች ለማሰብ እንሞክር።

ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ወንበር ስንይዝ።

  • ሙዚቃው ሊጀምር ሲል።

  • ስብሰባውን በምናደርግበት ከተማ ሆቴል ውስጥ ስናርፍ።

  • ፈቃደኛ ሠራተኞች ሆኖ በማገልገል።