በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

ሰዎች በክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የምንጋብዝበት ዘመቻ

ሰዎች በክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የምንጋብዝበት ዘመቻ

በየዓመቱ በክልል ስብሰባ ላይ የሚቀርብልንን የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ በጉጉት እንጠብቃለን። በመሆኑም ሌሎችም በዚህ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የይሖዋን ጥሩነት እንዲቀምሱ በተቻለን መጠን ብዙ ሰዎችን እንጋብዛለን። (መዝ 34:8) የእያንዳንዱ ጉባኤ የሽማግሌዎች አካል የመጋበዣ ወረቀቱን በሚገባ ለመጠቀም የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ ይወስናል።

በአእምሯችን ልንይዛቸው የሚገቡ ነገሮች

  • እኔ የምካፈልበት የክልል ስብሰባ የሚደረገው መቼ ነው?

  • በእኔ ጉባኤ ዘመቻው የሚጀምረው መቼ ነው?

  • የጉባኤዬ የመስክ አገልግሎት ስምሪት የሚደረገው መቼ መቼ ነው?

  • በዘመቻው ወቅት ግቤ ምንድን ነው?

  • እነማንን መጋበዝ እችላለሁ?

ምን ማለት ትችላላችሁ?

በአካባቢው የተለመደውን ሰላምታ ከሰጣችሁ በኋላ እንዲህ ማለት ትችላላችሁ፦

“በጣም አስፈላጊ በሆነ አንድ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ በዓለም ዙሪያ ሰዎችን እየጋበዝን ነው። ዝግጅቱ የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በዚህ የመጋበዣ ወረቀት ላይ ይገኛል። በዚህ ዝግጅት ላይ ከእኛ ጋር ቢገኙ ደስ ይለናል።”

የሰዎችን ፍላጎት መቀስቀስ የምትችሉት እንዴት ነው?

ግባችን በዚህ ስብሰባ ላይ ብዙ ሰዎችን መጋበዝ ቢሆንም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትለን ለመርዳት ጥረት ማድረግ እንዳለብን መርሳት አይኖርብንም።

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ከመጋበዣ ወረቀቱ ጋር መጽሔቶችን ማበርከት እንችላለን።