በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን ማበረታታት ትችላላችሁ

የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን ማበረታታት ትችላላችሁ

በየዓመቱ በምናከብረው የመታሰቢያ በዓል ላይ በርካታ የቀዘቀዙ ክርስቲያኖች ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች የሕይወትን ሩጫ መሮጥ ጀምረው የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ፍጥነታቸውን ቀንሰዋል፤ ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል አንዳንዶቹ ወደ ይሖዋ ተመለስ በተባለው ብሮሹር ላይ ተጠቅሰዋል። (ዕብ 12:1) ያም ቢሆን የቀዘቀዙ ክርስቲያኖች በልጁ ደም በገዛቸው በይሖዋ ፊት አሁንም ውድ ዋጋ አላቸው። (ሥራ 20:28፤ 1ጴጥ 1:18, 19) ታዲያ እነዚህን ሰዎች ወደ ጉባኤው እንዲመለሱ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው?

አንድ እረኛ ከመንጋው ተነጥላ የጠፋችን በግ ለማግኘት በትጋት እንደሚፈልግ ሁሉ የጉባኤ ሽማግሌዎችም የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን ፈልገው ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። (ሉቃስ 15:4-7) ይህም የይሖዋን ፍቅርና አሳቢነት ያንጸባርቃል። (ኤር 23:3, 4) ሽማግሌዎች ብቻ ሳይሆኑ ሁላችንም የቀዘቀዙትን ማበረታታት እንችላለን። የእነሱን ስሜት ለመረዳትና ደግነት ለማሳየት የምናደርገው ጥረት ይሖዋን ያስደስተዋል፤ ለእኛም ቢሆን እርካታ ያስገኝልናል። (ምሳሌ 19:17፤ ሥራ 20:35) በመሆኑም ማበረታታት የምትችሉት ሰው ይኖር እንደሆነ ለማሰብ ሞክሩ፤ ከዚያም ሳትዘገዩ እርምጃ ውሰዱ!

የቀዘቀዙትን አበረታቱ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አቢ የማታውቃትን አንዲት የይሖዋ ምሥክር ስታገኝ ምን አደረገች?

  • አንድን የቀዘቀዘ ሰው ለመርዳት ስናስብ ሽማግሌዎችን ማነጋገር ያለብን ለምንድን ነው?

  • አቢ ሎራን ለሁለተኛ ጊዜ ልትጠይቃት ስትሄድ ምን ዝግጅት አድርጋለች?

  • አቢ ሎራን ለማበረታታት ጥረት ስታደርግ ጽናት፣ ትዕግሥትና ፍቅር ያሳየችው እንዴት ነው?

  • በሉቃስ 15:8-10 ላይ ኢየሱስ ከተናገረው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?

  • ሎራን ለመርዳት የተደረገው ጥረት ምን በረከት አስገኘ?