በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 22-24

ይሖዋን የሚያውቅ ልብ አለህ?

ይሖዋን የሚያውቅ ልብ አለህ?

ይሖዋ ሰዎችን ከበለስ ጋር አመሳስሏቸዋል

24:5

  • ወደ ባቢሎን በግዞት ከተወሰዱት አይሁዳውያን መካከል ታማኝ የሆኑት በጥሩ በለስ ተመስለዋል

24:8

  • ታማኝ ያልሆነው ንጉሥ ሴዴቅያስና መጥፎ የሆነውን ነገር ያደርጉ የነበሩ ሌሎች አይሁዳውያን በመጥፎ በለስ ተመስለዋል

ይሖዋን የሚያውቅ ልብ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?

24:7

  • የይሖዋን ቃል ካጠናንና ቃሉን በተግባር ላይ ካዋልን ይሖዋ እሱን የሚያውቅ ልብ ይሰጠናል

  • ልባችንን በሐቀኝነት በመመርመር ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና አደጋ ላይ የሚጥሉ ዝንባሌዎችንና ምኞቶችን ነቅለን መጣል ይኖርብናል

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ይሖዋን የሚያውቅ ልብ አለኝ? እንዲህ ያለ ልብ ማዳበር የምችለው እንዴት ነው?