ከሚያዝያ 17-23
ኤርምያስ 25-28
መዝሙር 73 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ልክ እንደ ኤርምያስ ደፋሮች ሁኑ”፦ (10 ደቂቃ)
ኤር 26:2-6—ይሖዋ ኤርምያስን የማስጠንቀቂያ መልእክት እንዲያውጅ አዞት ነበር (w09 12/1 24 አን. 6)
ኤር 26:8, 9, 12, 13—ኤርምያስ ተቃዋሚዎቹን በመፍራት አልተርበደበደም (jr-E 21 አን. 13)
ኤር 26:16, 24—ይሖዋ ይህን ደፋር ነቢይ ጠብቆታል (w09 12/1 25 አን. 1)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ኤር 27:2, 3—መልእክተኞች ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ለምን ሊሆን ይችላል? ኤርምያስ ቀንበር የሠራላቸውስ ለምንድን ነው? (jr-E 27 አን. 21)
ኤር 28:11—ኤርምያስ፣ ሃናንያህ በተቃወመው ጊዜ የጥበብ እርምጃ የወሰደው እንዴት ነው? እኛስ ከእሱ ምሳሌ ምን እንማራለን? (jr-E 187-188 አን. 11-12)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ኤር 27:12-22
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) T-36 (የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የተባለው ትራክት)—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) T-36 ለተበረከተለት ሰው—ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) lv 7 አን. 4-5—የጥናቶቻችንን ልብ መንካት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አሳይ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“የመንግሥቱ መዝሙሮች ድፍረት ይሰጣሉ”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። የጉልበት ሠራተኞችን ያበረታታ መዝሙር የሚለውን ቪዲዮ አጫውት።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 8 አን. 8-13 እና “በዓለም ላይ በብዛት የታተሙ ጽሑፎች” የሚለው ሰንጠረዥ
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 31 እና ጸሎት