በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 25-28

ልክ እንደ ኤርምያስ ደፋሮች ሁኑ

ልክ እንደ ኤርምያስ ደፋሮች ሁኑ

ኤርምያስ ኢየሩሳሌም ልክ እንደ ሴሎ ድምጥማጧ እንደሚጠፋ ተናግሯል

26:6

  • የይሖዋን መገኘት የሚያመለክተው የቃል ኪዳኑ ታቦት በሴሎ ይቀመጥ ነበር

  • ይሖዋ ፍልስጤማውያን ታቦቱን ማርከው እንዲወስዱ የፈቀደ ሲሆን ታቦቱም ዳግመኛ ወደ ሴሎ አልተመለሰም

ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ኤርምያስን እንደሚገድሉት ዝተውበት ነበር

26:8, 9, 12, 13

  • ኤርምያስ ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን በተመለከተ የጥፋት መልእክት በማወጁ ምክንያት ሕዝቡ ያዘው

  • ኤርምያስ በሁኔታው ተስፋ ቆርጦ ወደኋላ አላለም

ይሖዋ ኤርምያስን ጠብቆታል

26:16, 24

  • ኤርምያስ እስከ መጨረሻው ደፋር መሆኑን አሳይቷል፤ ይሖዋም አልተወውም

  • አምላክ ደፋር በሆነው አኪቃም አማካኝነት ኤርምያስን ከጉዳት ጠብቆታል

ኤርምያስ የሚያውጀው መልእክት ሕዝቡን የሚያበሳጭ ቢሆንም በይሖዋ ድጋፍና ማበረታቻ ለ40 ዓመታት ያህል ይህን መልእክት ማወጁን ሊቀጥል ችሏል