ከሚያዝያ 3-9
ኤርምያስ 17-21
መዝሙር 88 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ይሖዋ አስተሳሰብህንና ምግባርህን እንዲቀርጸው ፍቀድ”፦ (10 ደቂቃ)
ኤር 18:1-4—ሸክላ ሠሪ በሸክላው ላይ ሥልጣን አለው (w99 4/1 22 አን. 3)
ኤር 18:5-10—ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ ሥልጣን አለው (it-2-E 776 አን. 4)
ኤር 18:11—በይሖዋ ለመቀረጽ ፈቃደኛ ሁን (w99 4/1 22 አን. 4-5)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ኤር 17:9—ልብ ምን ያህል አታላይ እንደሆነ የሚታየው እንዴት ነው? (w01 10/15 25 አን. 13)
ኤር 20:7—ይሖዋ በኤርምያስ ላይ የበረታውና ያሞኘው በምን መንገድ ነው? (w07 3/15 9 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ኤር 21:3-14
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች ተዘጋጅ፦ (15 ደቂቃ) “የመግቢያ ናሙናዎች” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የመግቢያ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉት ነጥቦች ላይ ተወያዩ። አስፋፊዎች የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የተባለው ትራክት ለተበረከተላቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ አበረታታ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (5 ደቂቃ) አማራጭ፦ በዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። (yb16 22) አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
“ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው”፦ (10 ደቂቃ) የሦስት ደቂቃ ንግግር በማቅረብ ክፍሉን ጀምር። ስቲቭ ገርደስ፦ የተደረገልንን አቀባበል መቼም ቢሆን አንረሳውም የሚለውን ቪዲዮ በማጫወት ክፍሉን ደምድም።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 7 አን. 19-23፣ “JW.ORG” የሚለው ሰንጠረዥ፣ “ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ለማዳረስ የተጠቀምንባቸው አንዳንድ ዘዴዎች” እና “የአምላክ መንግሥት ለአንተ ምን ያህል እውን ነው?” የሚለው ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 13 እና ጸሎት