በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው

ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው

ለእነማን? አዲሶችን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የምናውቃቸውን ጨምሮ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎችን ላይ ለሚገኙ ሰዎች በሙሉ ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረግ አለብን። (ሮም 15:7፤ ዕብ 13:2) በስብሰባዎቻችን ላይ ከሌላ አገር የመጡ የእምነት ባልንጀሮቻችን ወይም ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባ ላይ የተገኙ የቀዘቀዙ ክርስቲያኖች ይገኙ ይሆናል። እናንተ እንዲህ ባለው ሁኔታ ሥር ብትሆኑ ምን ሊሰማችሁ እንደሚችል ለማሰብ ሞክሩ። ሞቅ ያለ አቀባበል ቢደረግላችሁ ደስ አይላችሁም? (ማቴ 7:12) ታዲያ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊትና ካለቀ በኋላ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ተዘዋውራችሁ ሌሎችን ሰላም ለማለት ለምን ጥረት አታደርጉም? እንዲህ ማድረጋችሁ በስብሰባዎቻችን ላይ ሞቅ ያለ መንፈስና ፍቅር እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ይሖዋን ያስከብረዋል። (ማቴ 5:16) እርግጥ ነው፣ በስብሰባው ላይ የተገኘውን እያንዳንዱን ሰው ማነጋገር አይቻል ይሆናል። ሆኖም ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ካደረግን በስብሰባው ላይ የተገኘ ማንኛውም ሰው የእንግድነት ስሜት አይሰማውም። *

እንግዳ ተቀባይ መሆን ያለብን እንደ መታሰቢያው በዓል ባሉ ለየት ያሉ ዝግጅቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ጊዜያት ነው። አዲሶች፣ ክርስቲያናዊ ፍቅር በተግባር ሲገለጽ ሲያዩና እነሱም እንዲህ ያለውን ፍቅር ሲያጣጥሙ አምላክን ለማወደስና ከእኛ ጋር አብረው በእውነተኛው አምልኮ ለመካፈል ሊነሳሱ ይችላሉ።—ዮሐ 13:35

^ አን.3 የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች በስብሰባ ላይ የሚገኙ ከጉባኤ የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎችን ሰላም ማለት እንደሌለብን በግልጽ ያሳያሉ።—1ቆሮ 5:11፤ 2ዮሐ 10