አምላክ “ለሁሉም ሁሉንም ነገር” ይሆናል
ለይሖዋ ታማኝ የሚሆኑ ሁሉ ወደፊት አስደናቂ የሆነ ሕይወት ይኖራቸዋል። አምላክ ቃል ስለገባቸው ነገሮች ለሌሎች በደስታ ስንናገር ተስፋችን ለእኛም ይበልጥ እውን ይሆንልናል። በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ማብቂያ ላይ ይሖዋ “ለሁሉም ሁሉንም ነገር” ይሆናል፤ ይህን ጊዜ በዓይነ ሕሊናቸው እንዲስሉ ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት ባልንጀሮቹን አበረታቷቸዋል።
ወደፊት ከምናገኛቸው በረከቶች መካከል አንተን ይበልጥ የሚያጓጓህ የትኛው ነው? ለምንስ?
አምላክ የሰጣቸው ተስፋቸው እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ የሆንከው ለምንድን ነው?