በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለመታሰቢያው በዓል መዘጋጀት የምትችለው እንዴት ነው?

ለመታሰቢያው በዓል መዘጋጀት የምትችለው እንዴት ነው?

ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለመታሰቢያው በዓል ለመዘጋጀት የሚያስችል ተጨማሪ ጊዜ እናገኛለን። የመታሰቢያው በዓል የሚውለው ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት ከሆነ በዚያ ሳምንት የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አይኖርም። በዓሉ የሚውለው ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ደግሞ የሕዝብ ንግግር እና የመጠበቂያ ግንብ ጥናት አይኖርም። ታዲያ ይህን ተጨማሪ ጊዜ በተሻለ መንገድ ትጠቀምበታለህ? በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ይህን ልዩ በዓል ለማክበር አንዳንድ ዝግጅቶች ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ የታወቀ ነው። (ሉቃስ 22:7-13km 3/15 1) ያም ቢሆን ሁላችንም ለበዓሉ ልባችንን ማዘጋጀትም ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

  • በበዓሉ ላይ መገኘት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አሰላስል።—1ቆሮ 11:23-26

  • ከይሖዋ ጋር ስላለህ የግል ዝምድና ቆም ብለህ አስብ።—1ቆሮ 11:27-29፤ 2ቆሮ 13:5

  • የመታሰቢያው በዓል ስላለው ትርጉም የሚያብራሩ ጽሑፎችን አንብብ እንዲሁም አሰላስልባቸው።—ዮሐ 3:16፤ 15:13

አንዳንድ አስፋፊዎች ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ የሚገኘውን የመታሰቢያው በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ካነበቡ በኋላ ያሰላስሉበታል። ሌሎች ደግሞ በዚህ የስብሰባ አስተዋጽኦ ላይ በሚገኘው ሰንጠረዥ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች ያነብባሉ። ስለ መታሰቢያው በዓል እንዲሁም ይሖዋና ኢየሱስ ስላሳዩን ፍቅር የሚያወሱ የመጠበቂያ ግንብ ርዕሶችን የሚከልሱ ክርስቲያኖችም አሉ። ስለ መታሰቢያው በዓል የምታጠናበት መንገድ ምንም ይሁን ምን፣ እንዲህ ማድረግህ ከይሖዋና ከኢየሱስ ጋር ይበልጥ ለመቀራረብ ያስችልሃል።