በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ቆሮንቶስ 10-13

ይሖዋ ታማኝ ነው

ይሖዋ ታማኝ ነው

10:13

ይሖዋ ፈቃዱ ከሆነ ፈተናውን ሊያስወግደው ይችላል፤ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ “መውጫ መንገዱን” የሚያዘጋጀው፣ ፈተናዎችን በጽናት መቋቋም እንድንችል የሚያስፈልገንን ድጋፍ በመስጠት ነው።

  • በቃሉ፣ በቅዱስ መንፈሱና በሚያቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ አማካኝነት አእምሯችንን፣ ልባችንንና ስሜታችንን ያረጋጋልናል።—ማቴ 24:45፤ ዮሐ 14:16 ግርጌ፤ ሮም 15:4

  • በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሊመራን ይችላል። መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎችንና መሠረታዊ ሥርዓቶችን እንድናስታውስ እንዲሁም መውሰድ የሚገባንን የጥበብ እርምጃ እንድናስተውል ይረዳናል።​—ዮሐ 14:26

  • በመላእክቱ ተጠቅሞ ይረዳናል።​—ዕብ 1:14

  • የእምነት አጋሮቻችንን በመጠቀም ይረዳናል።​—ቆላ 4:11