በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የውይይት ናሙናዎች

የውይይት ናሙናዎች

●○○ መመሥከር

ጥያቄ፦ አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

ጥቅስ፦ ዘፍ 1:28

ለቀጣዩ ጊዜ፦ አምላክ ለሰዎች ያለውን ዓላማ እንደሚፈጽም እንዴት ማወቅ እንችላለን?

○●○ የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ አምላክ ለሰዎች ያለውን ዓላማ እንደሚፈጽም እንዴት ማወቅ እንችላለን?

ጥቅስ፦ ኢሳ 55:11

ለቀጣዩ ጊዜ፦ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸዋል?

○○● ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ

ጥያቄ፦ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸዋል?

ጥቅስ፦ መዝ 37:10, 11

ለቀጣዩ ጊዜ፦ አምላክ የሚያመጣቸውን በረከቶች ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ (ከመጋቢት 14–ሚያዝያ 7)፦

“የመጣነው በአንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ ልንጋብዝዎት ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ። ይህ በዓል የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ነው።” መጋበዣውን ስጠው። “ይህ የመጋበዣ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ይገልጻል። ከበዓሉ በፊት ባለው ሳምንት ደግሞ ልዩ ንግግር ይኖረናል፤ በዚያም ላይ ቢገኙ ደስ ይለናል።”

ፍላጎት ካሳየ ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?