በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 32-33

በረከት ለማግኘት እየታገላችሁ ነው?

በረከት ለማግኘት እየታገላችሁ ነው?

32:24-28

የይሖዋን በረከት ማግኘት ከፈለግን በሕይወታችን ውስጥ ከመንግሥቱ ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ቅድሚያ ለመስጠት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለብን። (1ቆሮ 9:26, 27) በዕድሜ የገፋው ያዕቆብ የተወው ምሳሌ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነቶቻችንን መወጣት ያለብን በምን መንፈስ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል። የይሖዋን በረከት ማግኘት አጥብቀን እንደምንፈልግ በሚከተሉት መንገዶች ማሳየት እንችላለን፦

  • ለጉባኤ ስብሰባዎች በሚገባ በመዘጋጀት

  • በአገልግሎት አዘውትሮ በመካፈል

  • በጉባኤ ውስጥ ሌሎችን ለመርዳት የምንችለውን ሁሉ በማድረግ

ያላችሁበት ሁኔታ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን፣ ይሖዋ እንዲረዳችሁ አዘውትራችሁ ጸልዩ፤ እንዲሁም ይሖዋን በትጋት በማገልገል የእሱን በረከት ለማግኘት ጥረት አድርጉ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የይሖዋን በረከት ለማግኘት በሕይወቴ ውስጥ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ የሚያስፈልገኝ በየትኞቹ አቅጣጫዎች ነው?’