በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ባዕዳን አማልክትን አስወግዱ’

‘ባዕዳን አማልክትን አስወግዱ’

ያዕቆብ የኖረው ይሖዋ ስለ ጣዖት አምልኮ ሕግ ከመስጠቱ በፊት ቢሆንም ሊመለክ የሚገባው ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። (ዘፀ 20:3-5) በመሆኑም ይሖዋ በነገረው መሠረት ወደ ቤቴል ሲመለስ ያዕቆብ፣ ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ጣዖቶቻቸውን ሁሉ እንዲያስወግዱ አዟቸዋል። ከዚያም ያዕቆብ ጉትቻዎችን (እንደ ክታብ ያሉ ነገሮች ሳይሆኑ አይቀሩም) ጨምሮ ጣዖቶቻቸውን አስወገደ። (ዘፍ 35:1-4) ይሖዋ፣ ያዕቆብ በወሰደው እርምጃ እንደተደሰተ ምንም ጥርጥር የለውም።

በዛሬው ጊዜስ ይሖዋን ብቻ ማምለክ የምንችለው እንዴት ነው? ዋነኛው መንገድ፣ ከጣዖት አምልኮ ወይም ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ካለው ማንኛውም ነገር መራቅ ነው። ይህ ደግሞ ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያላቸውን ዕቃዎች ማስወገድንና የመዝናኛ ምርጫችንን በጥንቃቄ መመርመርን ይጠይቃል። ለምሳሌ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘የምዝናናባቸው መጻሕፍት ወይም ፊልሞች ስለ ቫምፓየሮች፣ ዞምቢዎች ወይም እነዚህን ስለመሳሰሉ ነገሮች የሚያወሱ ናቸው? አስማትን፣ ድግምትን ወይም ሟርትን ምንም ጉዳት እንደሌለው መዝናኛ አድርገው ያቀርባሉ?’ ይሖዋ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር መራቅ አለብን።—መዝ 97:10

‘ዲያብሎስን ተቃወሙት’ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ፓሌሳ የተባለች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በሕይወቷ ውስጥ ምን ችግር አጋጥሟት ነበር?

  • ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር የተያያዘ ችግር ሲያጋጥመን የሽማግሌዎችን እርዳታ መጠየቃችን የጥበብ እርምጃ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እንዲሁም ወደ አምላክ ቅረቡ—ያዕ 4:7, 8

    የይሖዋን ጥበቃ ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ከየትኞቹ ነገሮች ሙሉ በሙሉ መራቅ አለባቸው?

  • ፓሌሳ ምን ቆራጥ እርምጃ ወስዳለች?

  • እናንተ በምትኖሩበት አካባቢ ከአጋንንት ተጽዕኖ መራቅ የሚቻልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?