ከሚያዝያ 2-8
ማቴዎስ 26
መዝሙር 19 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ፋሲካ እና የመታሰቢያው በዓል ያላቸው ተመሳሳይነትና ልዩነት”፦ (10 ደቂቃ)
ማቴ 26:17-20—ኢየሱስ የመጨረሻውን ፋሲካ ከሐዋርያቱ ጋር አከበረ (“የፋሲካ ማዕድ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 26:18፣ nwtsty)
ማቴ 26:26—በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚቀርበው ቂጣ የኢየሱስን ሥጋ ይወክላል (“ያመለክታል” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 26:26፣ nwtsty)
ማቴ 26:27, 28—በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚቀርበው የወይን ጠጅ የኢየሱስን ‘የቃል ኪዳን ደም’ ይወክላል (“የቃል ኪዳን ደሜ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 26:28፣ nwtsty)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ማቴ 26:17—ኒሳን 13 ‘የቂጣ በዓል የሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን’ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? (“የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 26:17፣ nwtsty)
ማቴ 26:39—ኢየሱስ “ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ” ብሎ የጸለየው ለምን ሊሆን ይችላል? (“ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 26:39፣ nwtsty)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 26:1-19
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር—ቪዲዮ፦ (4 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs 59 አን. 21-22 እና ተጨማሪ ሐሳብ 16
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (8 ደቂቃ)
የይሖዋ ወዳጅ ሁን—ቤዛው፦ (7 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም አስቀድመህ የመረጥካቸው ልጆች ወደ መድረክ እንዲወጡ ካደረክ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቃቸው፦ ሰዎች የሚታመሙት፣ የሚያረጁትና የሚሞቱት ለምንድን ነው? ይሖዋ ምን ተስፋ ሰጥቶናል? በገነት ውስጥ ማግኘት የምትፈልገው ማንን ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 6 እና “የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ” የሚለው ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 138 እና ጸሎት