በሰንበት መፈወስ
የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች የነበራቸው ዝንባሌ ኢየሱስን በጣም ያሳዘነው ለምንድን ነው? ምክንያቱም በሰንበት ሕግ ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ደንቦች በመጨመር ሕጉ እንደ ሸክም እንዲታይ አድርገዋል። ለምሳሌ በሰንበት ትንኝ መግደል የተከለከለ ነበር። በተጨማሪም አንድን የታመመ ሰው በሰንበት ቀን መርዳት የሚቻለው ለሕይወት የሚያሰጋ ሁኔታ ካጋጠመው ብቻ ነበር። በሌላ አባባል የተሰበረ ወይም የወለቀ አጥንት መጠገን ክልክል ነበር ማለት ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ የሃይማኖት መሪዎቹ እጁ ለሰለለው ለዚህ ሰው ምንም ዓይነት አሳቢነት ማሳየት አይፈልጉም ነበር።