ከሚያዝያ 30–ግንቦት 6
ማርቆስ 5-6
መዝሙር 151 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኢየሱስ በሞት ያጣናቸውን ሰዎች ከሞት ለማስነሳት የሚያስችል ኃይል አለው”፦ (10 ደቂቃ)
ማር 5:38—የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ሐዘን ያስከትላል
ማር 5:39-41—ኢየሱስ በሞት ያንቀላፉ ሰዎችን ለማስነሳት የሚያስችል ኃይል አለው (“ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማር 5:39፣ nwtsty)
ማር 5:42—ወደፊት የሚከናወነው ትንሣኤ ‘እጅግ እንድንደሰት’ ያደርገናል (jy 118 አን. 6)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ማር 5:19, 20—ኢየሱስ በዚህ ወቅት የሰጠው መመሪያ ከዚህ ቀደም አዘውትሮ ከሚሰጠው የተለየ የሆነው ለምንድን ነው? (“ንገራቸው” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማር 5:19፣ nwtsty)
ማር 6:11—“የእግራችሁን አቧራ አራግፉ” የሚለው አገላለጽ ምን ያመለክታል? (“የእግራችሁን አቧራ አራግፉ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማር 6:11፣ nwtsty)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማር 6:1-13
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን በመጠቀም ውይይቱን ጀምር። የjw.org አድራሻ ካርድን አስተዋውቅ።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመረጥከውን ጥቅስና ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ ያዘጋጀኸውን ጥያቄ ተጠቀም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs 36 አን. 23-24—የጥናቶቻችንን ልብ መንካት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አሳይ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“የማስተማሪያ መሣሪያዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው”፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ።
ከይሖዋ ድርጅት ማጽናኛ ማግኘት፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ የፔራ ቤተሰብ ያጋጠሙት አንዳንድ ችግሮች ምንድን ናቸው? እንዲጸኑ የረዳቸው ምንድን ነው? ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴያችንን ማቋረጥ የሌለብን ለምንድን ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 10 እና “አስደሳች ጉዞዎች” የሚለው ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 133 እና ጸሎት