በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 45-51

ይሖዋ የተሰበረን ልብ ችላ አይልም

ይሖዋ የተሰበረን ልብ ችላ አይልም

ዳዊት መዝሙር 51ን የጻፈው ከቤርሳቤህ ጋር የፈጸመውን ከባድ ኃጢአት አስመልክቶ ነቢዩ ናታን ካነጋገረው በኋላ ነው። ዳዊት ሕሊናው ስለወቀሰው በትሕትና በደሉን ተናዘዘ።—2ሳሙ 12:1-14

ዳዊት ኃጢአት ቢፈጽምም በመንፈሳዊ ማገገም ይችል ነበር

51:3, 4, 8-12, 17

  • ንስሐ ከመግባቱና ኃጢአቱን ከመናዘዙ በፊት ሕሊናው በጣም ረብሾት ነበር

  • አምላክን ማሳዘኑ ከፍተኛ ሥቃይ አስከትሎበት ነበር፤ ከዚህም የተነሳ አጥንቶቹ እንደደቀቁ ተሰምቶት ነበር

  • የይሖዋን ይቅርታ ለማግኘት፣ በመንፈሳዊ ለማገገምና ቀድሞ የነበረውን ደስታ መልሶ ለማጣጣም ጓጉቶ ነበር

  • ዳዊት፣ ይሖዋ የመታዘዝ ፍላጎት እንዲፈጥርለት በትሕትና ጠይቋል

  • ይሖዋ ኃጢአቱን ይቅር እንደሚለው እርግጠኛ ነበር