ሰኔ 27-ሐምሌ 3
መዝሙር 52-59
መዝሙር 38 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል”፦ (10 ደቂቃ)
መዝ 55:2, 4, 5, 16-18—ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ አስጨናቂ ሁኔታዎች አጋጥመውታል (w06 6/1 11 አን. 3፤ w96 4/1 27 አን. 2)
መዝ 55:12-14—የዳዊት ልጅና የቅርብ ወዳጁ በዳዊት ላይ አሴሩበት (w96 4/1 29 አን. 6)
መዝ 55:22—ዳዊት፣ ይሖዋ እንደሚረዳው እርግጠኛ መሆኑን ገልጿል (w06 6/1 11 አን. 4፤ w99 3/15 22-23)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
መዝ 56:8—“እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም” የሚለው አገላለጽ ትርጉም ምንድን ነው? (w09 6/1 29 አን. 1፤ w08 10/1 26 አን. 3)
መዝ 59:1, 2—ዳዊት ያጋጠመው ነገር ስለ ጸሎት ምን ያስተምረናል? (w08 3/15 14 አን. 13)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) መዝ 52:1–53:6
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) አንድ ትራክት አበርክት። ለምታነጋግረው ሰው በጀርባው ገጽ ላይ ያለውን ኮድ አሳየው።
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ትራክት ለወሰደ ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አሳይ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg ትምህርት 3 አን. 2-3—jw.org ላይ የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? የሚለውን ቪዲዮ በማስተዋወቅ ደምድም።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መዝሙር 56
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (7 ደቂቃ)
“አምላክ ረዳቴ ነው”፦ (8 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ወንድሞችና እህቶች ስሜታቸውን ሲገልጹ በማዳመጥ አድማጮች ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ፣ በተቻለ መጠን በርካታ ሰዎች በቀረቡት ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። (ሮም 1:12) አስፋፊዎች ተፈታታኝ ሁኔታ ሲገጥማቸው ከአምላክ ቃል እርዳታ ማግኘት እንዲችሉ የምርምር መርጃ መሣሪያውን እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) ia ምዕ. 14 አን. 1-13
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 121 እና ጸሎት