“ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል”
ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ ከባድ የሆኑ ፈተናዎች አጋጥመውታል። መዝሙር 55 እስከተቀናበረበት ጊዜ ድረስ የሚከተሉት ፈተናዎች አጋጥመውት ነበር . . .
-
ስድብ
-
ስደት
-
ከባድ የበደለኝነት ስሜት
-
የቤተሰብን አባል በሞት ማጣት
-
ሕመም
-
ክህደት
ዳዊት ሸክሙ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ በተሰማው ጊዜም እንኳ ሁኔታውን መቋቋም እንዲችል የረዳው ነገር ነበር። እንዲህ ዓይነት ስሜት ለሚሰማቸው ሰዎች በመንፈስ መሪነት ይህን ምክር ሰጥቷል፦ “ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል።”
ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
-
ምንም ዓይነት ችግር፣ የሚያስጨንቅ ሁኔታ ወይም የሚያሳስብ ነገር ሲያጋጥማችሁ ለይሖዋ ልባዊ ጸሎት አቅርቡ
-
ከይሖዋ ቃልና ከድርጅቱ መመሪያና ድጋፍ ለማግኘት ሞክሩ
-
ለችግሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚስማማ መፍትሔ ለማግኘት አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል ጥረት አድርጉ