ክርስቲያናዊ ሕይወት
“አምላክ ረዳቴ ነው”
መዝሙር 52-59 ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው የተሰማውን ስሜት የሚያሳይ ነው። ሆኖም ዳዊት አስጨናቂ ሁኔታ ባጋጠመው ጊዜም በይሖዋ ታምኗል። (መዝ 54:4፤ 55:22) በተጨማሪም ይሖዋን ለቃሉ አወድሶታል። (መዝ 56:10) እናንተስ ልክ እንደ ዳዊት በይሖዋ ትታመናላችሁ? አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥማችሁ አመራር ለማግኘት ወደ ቃሉ ዞር ትላላችሁ? (ምሳሌ 2:6) በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ የረዷችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?
-
ተስፋ ስትቆርጡ ወይም ስትጨነቁ
-
ስትታመሙ
-
ሌሎች ቅር ሲያሰኟችሁ
-
ስደት ሲደርስባችሁ