ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ቪዲዮዎችን ተጠቅሞ ማስተማር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ቪዲዮዎች የማየትና የመስማት ችሎታን በመማረክ የሰዎችን ልብ ሊነኩ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የሰዎችን ትኩረት ለመያዝና ትምህርቱ በአእምሯቸው ላይ እንዲቀረጽ ያስችላል። ይሖዋ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅሞ በማስተማር ረገድ ከሁሉ የላቀ ምሳሌ ትቷል።—ሥራ 10:9-16፤ ራእይ 1:1
አምላክ ስም አለው? የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው? እና መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? የሚሉት ቪዲዮዎች ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ትምህርት 2 እና 3ን ለማስጠናት እንዲረዱ ተብለው የተዘጋጁ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? እና በመንግሥት አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የሚሉት ቪዲዮዎች ደግሞ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠኑና በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ የሚያበረታቱ ናቸው። አንዳንዶቹን ረጃጅም ቪዲዮዎቻችንን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን በምናስጠናበት ፕሮግራም ውስጥ ልናካትታቸው እንችላለን።—km 5/13 3
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
-
ለምታነጋግሩት ሰው ልታሳዩት ያሰባችሁትን ቪዲዮ አስቀድማችሁ አውርዱ
-
በቪዲዮው ውስጥ መልስ የሚያገኙ አንድ ወይም ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጁ
-
ቪዲዮውን አብራችሁ ተመልከቱ
-
በዋና ዋና ነጥቦቹ ላይ ተወያዩ
እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
-
መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? ወደሚለው ቪዲዮ የሚወስደውን በትራክቶቻችን ጀርባ ላይ የሚገኘውን ኮድ አሳዩ
-
መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? የሚለውን ቪዲዮ አሳዩ፤ ከዚያም ትምህርት 3 ላይ በማተኮር ምሥራች የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ