በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የክርስቶስን ፈለግ በጥብቅ ተከተሉ

የክርስቶስን ፈለግ በጥብቅ ተከተሉ

ኢየሱስ ፈተና ወይም ስደት ሲያጋጥመን ልንከተለው የሚገባ ግሩም ምሳሌ ትቶልናል። (1ጴጥ 2:21-23) ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ ሥቃይ ሲያደርሱበትም እንኳ አጸፋ ከመመለስ ተቆጥቧል። (ማር 15:29-32) ኢየሱስን እንዲጸና የረዳው ምንድን ነው? የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር። (ዮሐ 6:38) በተጨማሪም ትኩረቱ ያረፈው ‘ከፊቱ በሚጠብቀው ደስታ’ ላይ ነበር።—ዕብ 12:2

በእምነታችን ምክንያት በደል ሲፈጸምብን ምን ምላሽ እንሰጣለን? እውነተኛ ክርስቲያኖች ‘በክፉ ፋንታ ክፉ አይመልሱም።’ (ሮም 12:14, 17) ክርስቶስ የደረሰበትን ፈተና ተቋቁሞ በማለፍ ረገድ የተወውን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ የአምላክን ሞገስ ስለምናገኝ ደስተኞች እንሆናለን።—ማቴ 5:10-12፤ 1ጴጥ 4:12-14

ትልቁ ነገር የይሖዋ ስም ነው የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • እህት ፖይትጺንገር ለብቻዋ ታስራ በነበረበት ወቅት ጊዜዋን በጥበብ የተጠቀመችበት እንዴት ነው?

  • እህት ፖይትጺንገርና ባለቤቷ በተለያዩ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ምን መከራ ደርሶባቸዋል?

  • እንዲጸኑ የረዳቸው ምንድን ነው?

መከራ ሲደርስባችሁ የክርስቶስን ፈለግ በጥብቅ ተከተሉ