ክርስቲያናዊ ሕይወት
ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ስኬታማ መሆን የሚችሉበትን ከሁሉ የተሻለ አጋጣሚ ስጧቸው
ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው ይሖዋን በታማኝነት ሲያገለግሉ ለማየት ይጓጓሉ። ወላጆች ይህን ምኞታቸውን ማሳካት የሚችሉት ልጆቻቸው ጨቅላ ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ በልባቸው ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች በመቅረጽ ነው። (ዘዳ 6:7፤ ምሳሌ 22:6) ይህ ከፍተኛ መሥዋዕትነት እንደሚጠይቅ ምንም ጥርጥር የለውም! ሆኖም እንዲህ በማድረጋቸው የሚያገኙት ወሮታ በጣም የሚክስ ነው።—3ዮሐ 4
ወላጆች ከዮሴፍና ከማርያም ብዙ ትምህርት ማግኘት ይችላሉ። ዮሴፍና ማርያም “በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው”፤ ይህ አድካሚና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ነገር ቢሆንም እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ አላሉም። (ሉቃስ 2:41) ለቤተሰባቸው መንፈሳዊነት ቅድሚያ ይሰጡ እንደነበር በግልጽ መረዳት ይቻላል። በዛሬው ጊዜ ያሉ ወላጆችም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው በቃል በማስተማርም ሆነ ምሳሌ ሆነው በመገኘት ልጆቻቸውን በትክክለኛው አቅጣጫ እንዲጓዙ ሊመሯቸው ይችላሉ።—መዝ 127:3-5
ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመውበታል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ጆን እና ሻረን ልጆቻቸውን በሚያሳድጉበት ጊዜ ከመንግሥቱ ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠት የቻሉት እንዴት ነው?
-
ወላጆች ለእያንዳንዱ ልጅ ተግሣጽ የሚሰጡበት መንገድ የተለያየ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?
-
ወላጆች ልጆቻቸው የእምነት ፈተናዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?
-
ልጆቻችሁ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ለመርዳት በይሖዋ ድርጅት የተዘጋጁትን የትኞቹን መሣሪያዎች ተጠቅማችኋል?