ክርስቲያናዊ ሕይወት
ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀሙ ወጥመድ ውስጥ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እንደ አብዛኞቹ መሣሪያዎች ሁሉ ማኅበራዊ ድረ ገጾችም ጠቃሚ ወይም ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ጨርሶ ላለመጠቀም ወስነዋል። ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ ከቤተሰቦቻቸውና ከወዳጆቻቸው ጋር ለመገናኘት ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ይጠቀማሉ። ሆኖም ዲያብሎስ ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ጥበብ በጎደለው መንገድ ማለትም ስማችንን ሊያጎድፍና መንፈሳዊነታችንን ሊጎዳ በሚችል መንገድ እንድንጠቀም ይፈልጋል። ልክ እንደ ኢየሱስ በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙትን መሠረታዊ ሥርዓቶች በመጠቀም አደገኛ ሁኔታዎችን ለይተን ማወቅና ከእነሱ መራቅ እንችላለን።—ሉቃስ 4:4, 8, 12
ልንርቃቸው የሚገቡ ወጥመዶች፦
-
ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ረጅም ሰዓት ማሳለፍ። ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ወይም ሚዲያዎችን በመጠቀም ረጅም ሰዓት ማሳለፋችን ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች የምናውለውን ውድ ጊዜ ሊሻማብን ይችላል
መሠረታዊ ሥርዓቶች፦ ኤፌ 5:15, 16፤ ፊልጵ 1:10
-
አጠያያቂ ምስሎችን መመልከት ወይም ጽሑፎችን ማንበብ። የፆታ ስሜት የሚቀሰቅሱ ምስሎችን መመልከት የብልግና ምስሎችን የማየት ሱስ እንዲይዘን ሊያደርግ ብሎም የፆታ ብልግና ወደ መፈጸም ሊመራን ይችላል። ከሃዲዎች ያዘጋጇቸውን ጽሑፎች ወይም በተለያዩ ድረ ገጾች ላይ ያሰፈሯቸውን ሐሳቦች ማንበብ እምነታችንን ሊሸረሽረው ይችላል
-
ተገቢ ያልሆኑ ሐሳቦችን መጻፍ ወይም ፎቶዎችን ማውጣት። ልብ አታላይ ስለሆነ አንድ ሰው በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ተገቢ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለመጻፍ ወይም ፎቶዎችን ለማውጣት ሊፈተን ይችላል። ሆኖም እንዲህ ማድረጉ ስሙን ሊያጎድፍበት ወይም መንፈሳዊነቱን ሊያዳክምበት ይችላል
ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ሁኔታዎች መከላከል የምትችለው እንዴት እንደሆነ ለማሰብ ሞክር፦