ክርስቲያናዊ ሕይወት
መዝናኛችሁን በጥበብ ምረጡ
መዝናኛችንን በጥበብ መምረጥ ያለብን ለምንድን ነው? በአንድ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ድረ ገጽ፣ መጽሐፍ ወይም የቪዲዮ ጨዋታ ለመዝናናት ስንመርጥ ወደ አእምሯችን የምናስገባውን ነገር እየመረጥን ነው። ምርጫችን በባሕርያችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የሚያሳዝነው በዛሬው ጊዜ ያለው አብዛኛው መዝናኛ ይሖዋ የሚያወግዛቸውን ነገሮች የያዘ ነው። (መዝ 11:5፤ ገላ 5:19-21) በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሖዋን የሚያስከብሩ ነገሮችን ሁልጊዜ እንድናስብ ያበረታታናል።—ፊልጵ 4:8
ምን ዓይነት መዝናኛ መምረጥ ይኖርብኛል? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
በጥንቷ ሮም ይካሄዱ የነበሩ የግላዲያተሮች ፍልሚያዎች በዘመናችን ካሉ አንዳንድ መዝናኛዎች ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?
-
ታዳጊዎችና ወጣቶች መዝናኛቸውን በጥበብ እንዲመርጡ የጉባኤው አባላት ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?
-
ሮም 12:9ን ከመዝናኛ ምርጫ ጋር በተያያዘ ግምት ውስጥ ማስገባት የምንችለው እንዴት ነው?
-
በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት ጤናማ መዝናኛዎች አሉ?