በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ገላትያ 4-6

“ምሳሌያዊ ትርጉም” ካላቸው ነገሮች የምናገኘው ትምህርት

“ምሳሌያዊ ትርጉም” ካላቸው ነገሮች የምናገኘው ትምህርት

4:24-31

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ አዲሱ ቃል ኪዳን ከሕጉ ቃል ኪዳን ያለውን ብልጫ ለማስረዳት “ምሳሌያዊ ትርጉም” ያላቸውን ነገሮች ተጠቅሟል። ፍቅር በሚንጸባረቅበት የክርስቶስና የተባባሪ ገዢዎቹ አስተዳደር ሥር፣ ሁሉም የሰው ዘሮች ከኃጢአት፣ ከአለፍጽምና፣ ከሐዘንና ከሞት ነፃ ይወጣሉ።—ኢሳ 25:8, 9

 

አጋር—ባሪያዪቱ ሴት

በሕጉ ቃል ኪዳን ሥር ያለችውንና ዋና ከተማዋን ኢየሩሳሌም ያደረገችውን እስራኤልን ትወክላለች

ሣራ—ነፃዪቱ ሴት

ላይኛዪቱን ኢየሩሳሌም ማለትም የአምላክን ድርጅት ሰማያዊ ክፍል ትወክላለች

የአጋር “ልጆች”

አይሁዳውያንን ይወክላሉ፤ የሕጉን ቃል ኪዳን ለማክበር ቃል የገቡት እነዚህ ሰዎች፣ ኢየሱስን ያሳደዱት ከመሆኑም ሌላ አልተቀበሉትም

የሣራ “ልጆች”

ክርስቶስና 144,000ዎቹ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች

የሕጉ ቃል ኪዳን ያስከተለው ባርነት

ሕጉ፣ የኃጢአት ባሪያዎች እንደሆኑ እስራኤላውያንን ያስታውሳቸው ነበር

አዲሱ ቃል ኪዳን ነፃነት ያስገኛል

የክርስቶስ መሥዋዕት ባለው ዋጋ ማመን ሕጉ ካስከተለው ኩነኔ ነፃ አውጥቷቸዋል