ክርስቲያናዊ ሕይወት
የውይይት ናሙናዎችን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
ከጥር 2018 አንስቶ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን—የስብሰባው አስተዋጽኦ በሽፋኑ ላይ የውይይት ናሙናዎች ይዞ ሲወጣ ቆይቷል። እነዚህን የውይይት ናሙናዎች መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
የተማሪ ክፍል ስናቀርብ፦ በውይይት ናሙናው ላይ የሚገኘውን ጥያቄ፣ ጥቅስ እና ለቀጣዩ ጊዜ የተዘጋጀውን ጥያቄ መጠቀም ይኖርብናል። ይህ ሲባል ግን በውይይት ናሙና ቪዲዮው ላይ ያለውን አቀራረብ ቃል በቃል መድገም አለብን ማለት አይደለም። የተለየ መቼት፣ መግቢያ ወይም ማብራሪያ መጠቀም እንችላለን። በተጨማሪም ለክፍሉ በተሰጠው መመሪያ ላይ በቀጥታ ባይገለጽም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ከሚገኙት ጽሑፎች አንዱን ማበርከት እንችላለን።
በአገልግሎት ላይ፦ የውይይት ናሙናዎቹ የተዘጋጁት መነሻ ሐሳብ እንዲሰጡን ታስበው ነው። ያነጋገርነው ግለሰብ ፍላጎት ካሳየ እንዲሁም ስለ ጉዳዩ ይበልጥ ማወቅ ከፈለገ ውይይቱን ማቋረጥ አያስፈልገንም፤ ምናልባትም ለተመላልሶ መጠየቅ የተዘጋጀውን የውይይት ናሙና ተጠቅመን ውይይቱን መቀጠል እንችላለን። የውይይት ናሙናውን በመጠኑ መቀየር ወይም ሙሉ በሙሉ የተለየ አቀራረብ መጠቀም እንችላለን። የክልላችንን ሰዎች የሚማርከው ለሌላ ወር የተዘጋጀ የውይይት ናሙና ወይም ሌላ ጥቅስ ይሆን? በአካባቢያችን የተፈጠረ ክንውን ወይም አንድ ዜና በክልላችን የሚገኙትን ሰዎች ትኩረት ይበልጥ ይስብ ይሆን? የውይይት ናሙናዎቹን የምንጠቀምበት መንገድ ምንም ይሁን ምን ግባችን ‘ምሥራቹን ለሌሎች እናካፍል ዘንድ ለምሥራቹ ስንል ሁሉን ነገር ማድረግ’ ሊሆን ይገባል።—1ቆሮ 9:22, 23